‹‹ቃሊቲ››ን በጨረፍታ
ክፍል ሶስት…..በተመስጌን ደሳለኘ
ድንግርግር አለኝ፡፡ ይህን ጊዜ ዕቃዬን ይዞልኝ የመጣው ወጣት በስሜ ጠርቶ ‹‹አይዞህ›› አለኝ፡፡ ድጋሚ መገረም ጫረብኝ፡፡ ስሜን አልነገርኩትም፡፡ የፖሊስ ኃላፊውም እንዳልነገረው አስታውሳለሁ፡ ፡ ታዲያ እንዴት አወቀኝ? ‹‹ታውቀኛለህ እንዴ?›› ስል ጠየኩት፡፡ እንደሚያውቀኝ ራሱን ወደላይና ታች አወዛውዞ ገለፀልኝ፡ ፡ እዚያ ግቢው ውስጥ በሚገኝ ላይብረሪ ፍትህ ጋዜጣ አልፎ አልፎ እንደሚመጣ እኔንም አንገቴ ላይ በጠመጠምኩት ሻርፕ በቀላሉ ሊለየኝ እንደቻለ አጫወተኝ፡፡
ስድስት ቀናትን ስላሳለፍኩበት የ‹‹ቃሊቲ እስር ቤት›› የእስረኞች አቀባበልና አያያዝ ምን መልክ እን

ዳለው
ጨርፌ ማሳየት ከጀመርኩ ይህ ፅሁፍ ሶስተኛው ክፍል ላይ መድረሴን ያበስራል፡፡ ከዚህ በኋላም ለአንድ ሁለት ክፍል
ያህል በትርክቱ ላይ መቆየቴ አይቀሬ ነው፡፡ …እነሆም የዛሬውን ትርክት ባለፈው አስራ አምስት ቀን ካቆምኩበት
እቀጥላለሁ፡ ፡
…ምጥጥ ያለ ፊት እና መካከለኛ ቁመት ያለው የፖሊስ ኃላፊ ባልተለመደ ሰዓት (ለስንቅ እና ለመፀዳጃ ቤት ከሚከፈትበት ጊዜ በተለየ) ጨለማ ቤቷን ከተሸጎረችበት ጓጉንቸር ነፃ አውጥቶ ወለል አደረጋት፡፡ ለስለስ ያለ ሙቀት አዘል የፀሐይ ጨረር ክፍሏን ወገግ አደራግት፡፡ ‹‹ዕቃህን ይዘህ ውጣ›› የሚለው ትዕዛዙም በጎርናና ድምፅ ተከተለ፡፡ ከተጋደምኩበት ፍራሽ ላይ ተነስቼ አስተዋልኩት፡፡ ፊቱ ላይ የሚነበብ ነገር የለም፡፡ መፈታቴ እንዳልሆነ ስሜቴ ነግሮኛል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በቆየበት ጊዜያት የዘመናት የአልጋ ቁራኞችን ‹‹አልጋህን ይዘህ ተነሳ!›› ይል ነበር፡ ፡ በእርግጥ ይህ ቃል እንደፖሊሱ ‹‹ትዕዛዝ›› ሳይሆን፣ ፈውስ እንደነበረ የቆየ ንባቤ ያስታውስኛል፡፡ ህይወት አልባ መሳይ ፊት ያለው የፖሊስ ኃላፊ እቃዬን ይዤ እንድወጣ እየጠበቀኝ ነው፡፡ ፍራሽ፣ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ጥቂት ቅያሪ ልብሶች፣ አንድ የምሳ ዕቃ… አንድ ላይ ሸክፌ ለመሸከም ተወለካከፍኩ፡፡ ስሰበስበው ተበተነ፡ ፡ መልሼ ሰበሰብኩት፡፡ ‹‹ተከተለኝ››፡ ፡ ‹‹የት ድረስ?›› ብዬ ልጠይቀው አሰብኩና ተውኩት፡፡ ተከተልኩት፡ ፡ ከነበርንበት ግቢ ወጥተን ሌላ ግቢ ውስጥ ገባን፤ ግቢው ከአቅሙ በላይ በሰው ጎርፍ ተጥለቅልቋል፡ ፡ ጫጫታው ከደራ ገበያ ጫጫታ ይበረታል፡፡ ግቢውን አቋርጠን ሌላ ግቢ ውስጥ ገባን፡፡ ኋላ ላይ እንደሰማሁት ያ ጫጫታም ግቢ ከአሰቃቂው የቃሊቲ የእስር ዞኖች ሁሉ የከፋ እንደሆነ የሚነገርለት ዝነኛው ‹‹ዞን ሶስት›› ነው፡፡ (በነገራችን ላይ ቃሊቲ ውስጡ በዘጠኝ ዞኖች የተከፋፈለ ነው፡ ፡ በክልል ቢከፋፍሉት ኖሮ ከስርዓቱ ርዕዮተ-አለም ጋር የተመጣጠነ ትርጓሜ ይኖረው ነበር፡፡ ታላቋን ኢትዮጵያ በዘጠኝ ቁርጥራጭ ክልሎች ከከፋፈለው አብዮታዊ ዴሞክራሲ ርዕዮተ ዓለም አኳያ ማለቴ ነው)
ዞን ሶስትን እንደማሳለጫ ተጠቅመን ጥቂት ከተጓዝን በኋላ በመጠኑም ቢሆን እስከአሁን ካየኋቸው ግቢዎች ሁሉ አይንን የሚማርክ ግቢ በር ላይ ደረስን፡፡ በዕውቀቱ ስዩም ‹‹አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤ ስትገቡም ሌላ በር ይጠብቃችኋል›› እንዲል በአንዱ በር ስንገባ፣ ሌላ በር ሲጠብቀን፤ ስንተላለፍበት-ሌላ በር ስናገኝ… ስንገባ-ስንወጣ… ነው ከእዚህ አይነ-ግቡ ግቢ የደረስነው፡፡ ግቢው ስፋቱ አነስተኛ ቢሆንም ከነዋሪዎቹ (ከእስረኞቹ) አኳያ ሲታይ ተመጣጣኝ ነው፡፡ በእንክብካቤ የተያዙ አበቦችም አሉት፡፡ እንደዞን ሶስት ጫጫታ የለበትም፡፡ እየመራ ያመጣኝ የፖሊስ ኃላፊ ከግቢው በር ላይ ‹‹በስራ- ፈትነት›› የቆመ አንድ እስረኛን ‹‹አግዘው!›› አለና እቃዬን እንዲቀበለኝ አደረገ፡፡ ይህ ትዕዛዝ ያመላከተኝ ነገር የፖሊሱን ደግነት ሳይሆን ኢየሱስ መስቀል ተሸክሞ እየወደቀና እየተነሳ መጓዙ ያሰለቻቸውና ከዋና ጉዳያቸው ያዘገያቸው የሮማ ወታደሮች በመንገድ ላይ ያገኙትን ስምኦን የተባለ የ‹‹ቀሬና›› ሰውን ‹‹አግዘው›› ብለው ጉዞአቸውን እንዳፈጠኑት አይነት ትብብር ነው፡፡ ፖሊሱም ‹‹አግዘው›› ብሎ ተቻኩሎ ወደአዲሱ ማረፊያዬ በቶሎ አስገብቶኝ ሊመለስ ተጣድፏል፡፡ … ምን አጣድፎት ይሆን? የት ለመሄድ ይሆን እንዲህ የቸኮለው? የሚል ሃሳብ ሽው አለብኝ፡፡ ብቻ አግዘው የተባለው ወጣት እስረኛ እንደከተፎ ሰራተኛ እንዲያ ለሸክም አስቸገሮኝ የነበረውን ዕቃ በቀላሉ ለብቻው ጠቅልሎ ያዘው ‹‹ተው ተካፍለን እንያዝ›› ብለውም በጅ አልል አለ፡፡ ደክሞኝ ስለነበር ጥቂት አግደርድሬ ተውኩለት፡፡ ይህን ጊዜ ፖሊሱ አጠገባችን እንደቆሙ እስከአሁን ወላላስተዋልኳቸው አንድ ጠና ያሉ ሰው ዞሮ ‹‹አዲስ እስረኛ ነው፤ አልጋ ስጡት!›› አላቸውና ፊቱን አዙሮ ሄደ፡፡ የተረከቡኝ ሰውዬ ጥቂት ካስተዋሉኝ በኋላ ‹‹እስር ቤት እንኳን ደህና መጣህ ባይባልም ይህ ግቢ እዚህ ካሉት ሌሎች ዞኖች በእጅጉ የተሻለ ነው፤ እንተዋወቅ እኔ እስረኛ ብሆንም የግቢው እስረኞች ኃላፊ ነኝ፡ ፡ ሻምበል በጋሻው አታላይ እባላለሁ›› አሉና እጃቸውን ዘረጉልኝ፡፡
በመደነቅ አስተዋልኳቸው፡፡ ሻምበል በጋሻውን በስም እና በታሪክ በደንብ አውቃቸዋለሁ፡፡ የደርግ አባል እና የቀድሞ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ነበሩ፡፡ የሚገርም ነው፡፡ መንግስቱ ኃይለማርያምም ታስሮ ቢሆን ኖሮ ዛሬ በእንዲህ አይነት ሁኔታ አገኘው ነበር፡፡ ባገኘው ብዙ የምጠይቀው ጥያቄዎች ነበሩኝ፡፡ መሪዎቻችን ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ቢያንስ ለታሪክ እና ለተተኪው ትውልድ ትምህርት ይሆን ዘንድ ሊመልሱልን የሚገቡ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ አልታደልንም፡፡ እነሱም ለመመለስ ዕድሉን አላገኙም፡ ፡ መንግስቱ ኃ/ማርያም ከጥያቄም ከፍርድም አምልጦ ዚምባብዌ ከሚባል ሀገር ተደብቋል፡፡ መለስ ዜናዊም ቢሆን በተፈጥሮ ሞት ህይወቱ አልፏል፡፡ ሀገሪቷም ገና ‹‹ከሀዘኗ›› አልተላቀቀችም፡፡ ሁኔታው ሁሉ በህይወት ሳለ አካባቢውን በመበጥበጥ ለያዥ ለገናዥ አስቸጋሪ የነበረው ልጅ ህይወቱ ካለፈ በኋላ እናቱ ‹‹የሞተው ልጄ አንገቱ ረጅም ነበር›› አለች እንደተባለው አይነት ውዳሴ-ከንቱ ኢትዮጵያ ሀገሬም አምባገነን መሪዋን ‹‹ባለራዕዩ፣ ታላቁ፣ መልዐኩ፣ አዛኙ፣ ርህሩህ፣ ሰው ወዳዱ፣ ዴሞክራቱ፣ የልማት አርበኛው…›› ወዘተርፈ የሚል ማንቆለጳጰሻ ካባ ደርባ ‹‹እያለቀሰች›› ነው፡፡ እንግዲህ የሞተ ሰው አንዴ ሄዷል-አይመለስም፡፡ እኛ ወደ እርሱ እንሄዳለን እንጂ እሱ ዳግም ተመልሶ ወደኛ አይመጣም፡፡ …እናም በአፀደ-ህይወት ያለነው እንነጋገር፡፡
…አዛውንቱ በጋሻው አታላይ እየመሩ መጋዘን ወደ መሰለ ሰቀላ ቤት ይዘውኝ ገቡ፡፡ ቤቱ ሰፊ ነው፡፡ በልማት ስም ከፈረሰው የቀበሌያችን አዳራሽም ይሰፋል፡፡ በድርብርብ አልጋዎች ከመሞላቱ የተነሳ እልም ያለ ዋሻ- ባለብዙ ሽንቁሮች መስሏል፡፡ ሆኖም አልተጨናነቀም፡፡ ሻምበሉ ወደአንድ ባዶ አልጋ እየጠቆሙኝ ‹‹የላይኛው የአንተ ነው፡፡ ወደፊት አልጋ ሲለቀቅ ከስር እንቀይርልሃለን፡፡ እቃህን ከላይ መስቀል ትችላለህ፡፡ መልካም ቆይታ ይሁንልህ›› አሉና ተሰናብተውኝ ሄዱ፡ ፡
ድንግርግር አለኝ፡፡ ይህን ጊዜ ዕቃዬን ይዞልኝ የመጣው ወጣት በስሜ ጠርቶ ‹‹አይዞህ›› አለኝ፡፡ ድጋሚ መገረም ጫረብኝ፡፡ ስሜን አልነገርኩትም፡ ፡ የፖሊስ ኃላፊውም እንዳልነገረው አስታውሳለሁ፡፡ ታዲያ እንዴት አወቀኝ? ‹‹ታውቀኛለህ እንዴ?›› ስል ጠየኩት፡፡ እንደሚያውቀኝ ራሱን ወደላይና ታች አወዛውዞ ገለፀልኝ፡ ፡ እዚያ ግቢው ውስጥ በሚገኝ ላይብረሪ ፍትህ ጋዜጣ አልፎ አልፎ እንደሚመጣ እኔንም አንገቴ ላይ በጠመጠምኩት ሻርፕ በቀላሉ ሊለየኝ እንደቻለ አጫወተኝ፡፡ አያያዘናም ትላንትና በአሜሪካ እና በጀርመን ድምፅ ራዲዮ ቤተሰቦቼ እና የስራ ባልደረቦቼ ከታሰርኩ ጀምሮ አይተውኝ እንደማያውቁ፣ የት እንደደረስኩ ባለማወቃቸውም ስጋት ላይ መውደቃቸውን ሲናገሩ መስማቱን ጨምሮ ነገረኝ፡፡ በመጨረሻም ለስንብት ሰላምታ እጁን እየዘረጋልኝ እርሱም እዚሁ ክፍል እንደታሰረና ከምሳ በኋላ እንደምንገናኝ ቀጠሮ አስይዞኝ ሄደ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ከመጀመሪያው የዕስር ቤት ደባሌ ጋር መተዋወቄ እንደሆነ ገባኝ፡፡ ባዶው አልጋ ላይ ፍራሼን ዘረጋሁበትና የያዙኩትን ዕቃ ደረደርኩ፡፡
እየተረኩልህ ያለሁት ግቢ ‹‹ዞን አራት›› ይባላል፡፡ የደርግ እስረኞች የታሰሩበት ነው፡፡ በእርግጥ አመቱ መጀመሪያ አካባቢ አብዛኞቹ ባለስልጣናት በምህረት ተለቀዋል፡፡ ፍሰሃ ደስታ፣ ፍቅረስላሴ ወግደረስ፣ ለገሰ አስፋው፣ ተስፋዬ ወ/ስላሴ፣ እንዳለ ተሰማ፣ አለሙ አበበ፣ ደበላ ዴንሳ…. ሁሉም እዚህ ዞን ውስጥ ነበሩ፡፡ ሊፈቱ አንድ ቀን ሲቀራቸው ህይወታቸው እንዳለፈ ከተነገረው ከደህንነት ሚኒስትሩ ተስፋዬ ወ/ ስላሴ በስተቀር ሌሎቹ ተፈተዋል፡፡ መፈታታቸውም ፖለቲካ መሆኑ ቀርቶ የመለስን መሀሪነት መስበኪያ ሆኗል፡ ፡ ግና በቃሊቲ መታሰር የሌለባቸው ንፁሃን በብዛት መኖራቸውን ምን እንለው ይሆን?
የሆነ ሆኖ እነዚያን ‹‹ምህረት- የለሽ›› እና ‹‹አስፈሪ›› እንደሆኑ የሚነገርላቸውን የደርግ ባለስልጣናት አግኝቼ ባወራቸው ብዬ ተመኘሁ፡፡ ለገሰ አስፋውን ስለሀውዜን ጭፍጭፋ እና ትግራይን ለህወሓት አስረክበው ስለመጡበት ሁኔታ ባወራቸው፣ ተስፋዬ ወልደስላሴን ደግሞ በአሉ ግርማን የት እንዳደረሱት ብጠይቃቸው፣ ለህወሓትም፣ ለሲ.አይ. ኤም፣ ለኬጂቢም፣ ለሞሳድም… ይሰሩ እንደነበረ ስለሚናፈሰው ጉዳይም አንዳንድ ነገሮችን ቢነገሩኝ ደስታዬን አልችለውም ነበር፡፡ ለፍቅረስላሴ ወግደረስም ቢሆን ብዙ ጥያቄዎች ነበሩኝ፡፡ ሙስና ‹‹ከጥሬ ስጋ እና ውስኪ›› ባላለፈበት በዛ የዋህ ዘመን ባለቤታቸው 25 ኪሎ ግራም ወርቅ ይዘው ቦንቤይ አየር ማረፊያ ተያዙ መባሉ ምን ያህል እውነት እንደሆነ እጠይቃቸው ነበር፡ ፡ መቼስ ‹‹አለባበስ እንደፍቅረስላሴ ወግደረስ›› የተባለላቸው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ብዙ የሚያውቁት ምስጢር ሳይኖር አይቀርም፡፡ ‹‹ቀይ ሽብር›› እንዲቆም ስለማድረጋቸው የተነገረላቸውን፣ ሆኖም በቀይ ሽብር የተከሰሱትን ደበላ ዴንሳንም አግኝቼ ከእርሳቸው አንዳንድ ማብራሪያ ባገኝ እልል በቅምጤ ነበር፡፡ በነገራችን ላይ ደርግ የመሰረተው መንግስትም ሆነ ቢሮክራሲው በእጅጉ ውስብስብ እንደነበረ ይነገራል፡፡ ይህ የደርግ መንግስት ከኃይለስላሴም ሆነ ከመለስ መንግስት ሁሉ የበረታ ነው ይባልለት ነበር፡፡ እንዲያውም አንድ ወዳጄ ኢህአዴግ አዲስ አበባ ሲገባ የደርግ መንግስት ከጠበቀው በላይ የተደራጀ እና ጠንካራ እንደነበር መረዳቱ ምን ያህል አስደንግጦት እንደነበረ አውግቶኛል፡፡ በዚህ ሰው አባባል መሰረት በዚያን ጊዜ መንግስት መስርቶ ከማቆም ራስ ዳሽን ተራራን ከቦታው አንስቶ ባሕር መክተት ይቀላል፡፡ ይሄ ውስጥ አወቅ ወዳጄ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም ህይወቱ ያለፈው አዲስ መንግስት ሲገነባ ነው ብሎ አርድቶኛል፡፡ ዳሩ ሃያ አንድ አመት ቢለፋም ከግብ አላደረሰውም፡ ፡ ስራው ከባድ ነው መሰለኝ፡፡ ያውም ከዜሮ ሲጀመር፡፡ ያውም ሁሉን የሚጠቀልል…
ለነገሩ መንግስቱ ኃይለማርያም መንግስት ለመመስረት የመለስን ያህል የለፋ አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም መንጌ ኃይለስላሴን አውርዶ ሹማምንቶቻቸውን በጥይት ከመፍጀቱ ውጪ የነበረውን መንግስታዊ መዋቅርና ተቋማት አጠናክሮ ነበር ይዞ የቀጠለው፡፡ ከስም ለውጦች እና ከአንዳንድ አብዮታዊ እርምጃዎች (መሬት፣ ሀይማኖት፣ ብሄር…) በቀር፡፡ በንጉሱ እና ቤተሰባቸው ስም ተሰይመው የነበሩ ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ አካባቢዎች፣ መንግደች… ወዘተ በአብዮታዊ ስም ከመቀየር ባለፈ ያፈረሰው ነገር አልነበረም፡፡ ምንአልባትም አፄው ከስልጣን በወረዱ ጊዜ ለመንግስቱና ለጓዶቹ እንዲህ ሲሉ መከሯቸው የተባለው ምክር በልቦናቸው አድሮ ይሆናል ‹‹ሁላችሁም ልጆች ናችሁ፤ የሰራችሁት የልጅነት ስራ ነው፤ ስለሀገራችሁ የምታውቁት ነገር የለም፤ ሀገሪቷን እንዳታጠፏት!››
መለስና ኢህአዴግ ጋ ግን ይህ የለም፡ ፡ መንግስቱንም መማረክ አልቻሉምና የአፄውን ምክር አላስተላለፈላቸውም፡ ፡ እናም ከሰራዊቱ እስከ ቢሮክራሲው ስሮ ተፈንቅሎ እና ፈርሶ ነው በአዲስ የተመሰረተው፡፡ ጦር ሰራዊት፣ ባህር ኃይል፣ አየር ኃይል፣ አየር ወለድ፣ ፓራ ኮማንዶ፣ እስፓርታ… ማን የቀረ አለ? ህንፃ ኮንስትራክሽን፣ ባህር ትራንዚት፣ አውራ ጎዳና፣ የዩኒቨርስቲ መምህራን…. ይህን ሁሉ እንደአዲስ ለማቆም ሲል ኢህአዴግ እንዲህ ያለ ይመስለኛል ‹‹ኑ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር እንፍጠር፤ በብሔር ብሔረሰቦችም እንሙላት››
የሆነ ሆኖ ከታሳሪዎች እንደሰማሁት ‹‹ዞን አራት›› ለሌሎች ዞኖች የሸራተንን ያህል የቅንጦት ቦታ ነው፡፡ መጨናነቅ የለም፤ ግቢው ንፁህ ነው፤ የተሻለ ላይብረሪ እና ካፍቴሪያ አለው፡ ፡ ግቢው ውስጥ ዘጠኝ የተለያዩ ቤቶች ቢኖሩም በአጠቃላይ የእስረኛው ቁጥር (እኔ በነበርኩበት ግዜ) አንድ መቶ ሰላሳ አምስት ብቻ ነው፡፡ ተመሳሳይ ስፋት ያለው ዞን ሶስት ግን ከሁለት ሺ የማያንስ እስረኛ እንደሚታጎርበት ታስሮበት የነበረ አንድ እስረኛ አጫውቶኛል፡፡ ቦታው የስቃይ ቦታ መሆኑን የሚያጠናክርልህ ሰሞኑን ከአንድ ዓመት በላይ ታስረው በምህረት የተለቀቁት ስውዲናዊያን ጋዜጠኞች ‹‹የመከራ ቋት›› ሲሉ ቃሊቲን በከፍተኛ ምሬት መግለፃቸው ነው፡ ፡ ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ በ2002 ዓ.ም የፋሲካ በአል ዋዜማ የ‹‹ፕሪዝን ፊሎ ሽፕ›› መስራች ፓስተር ዳንኤል ቃሊቲ ብቅ ብለው ብርቱካን ሚደቅሳን ሲጠይቋት በኢቲቪ በተመለከትኩበት ዕለት ስለእስር ቤቱ የሰጡት ምስክርነት ከዚህ የተለየ ነበር፡፡ ፓስተሩ ቃል በቃል ‹‹የእስር ቤቱ ጥራት በአፍሪካ ተወዳዳሪ የለውም›› ነበር ያሉት፡፡ አስታውሳለሁ፤ በእጅጉ አዝኜ ነበር፡፡ በእርግጥ አዝኜ ብቻ ዝም አላልኩም ‹‹ፓስተር ዳንኤል ለቄሳር ወይስ ለኢየሱስ?›› በሚል ርዕስ ትዝብቴን ፍትህ ጋዜጣ ላይ አስፍሬ ነበር፡፡
በአጠቃላይ ዞን አራት ቃሊቲ ከሚገኙ ሁሉም ዞኖች የተሻለ እንደሆነ እስረኞች እያዳነቁና እያጋነኑ ሲናገሩ ሰምቻለሁ፡፡ ወደዚህ ዞን ለመቀየር ያለው መከራም እንዲሁ ከባድ እንደሆነ አስተውያለሁ፡፡ እንዲያውም አንዳንድ እስረኞች ‹‹መታሰሬን›› ችላ ብለው ወደዞን አራት በመላኬ ብቻ ምን ያህል እድለኛ እንደሆንኩ ደጋግመው ነግረውኛል፡፡ በነገራችን ላይ በዚህ ዞን የሚገኙ እስረኞች ተራ ቀማኞች ወይም እንደእኔ ተራ ጋዜጠኞች እንዳይመስሉህ፡፡ አብዛኞቹ በአንድ ወቅት ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣን እና በተለያየ ኃላፊነት ላይ የነበሩ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ ከበርቴዎች ናቸውና፡፡
መቼም ቃሊቲ ያለውን እስረኛ ብዛት ላስተዋለ ቦታውን እስር ቤት ከማለት ይልቅ ‹‹መንግስትና ባንዲራ›› የሌለው አነስተኛ ሀገር ማለት ይቀላል፡፡ የእስረኛውን ብዛት ሳይ ከዚህ ቀደም አንድ ወዳጄ ‹‹አሜሪካ ወይም አውሮፓ ሄዷል ብለህ ያሰብከውን ሰው ቃሊቲ ልታገኘው ትችላለህ›› ሲል የነገረኝ ትዝ አለኝ፡፡
እቃዬን ደርድሬ ስጨርስ ከአዳራሹ ወጣሁ፡፡ ግቢ ውስጥ አንድ ወጣት እና አንድ ጎልማሳ ጠረጴዛ ቴኒስ ሲጫወቱ የተወሰኑ ሰዎች ዙሪያውን ቆመው ያያሉ፤ ወይም ለመጫወት ተራ እየጠበቁ ሊሆን ይችላል፡፡ አንድ አነስተኛ ጠረጴዛ ከበው ዳማ የሚጫወቱ እስረኞችም ይታዩኛል፡፡
በስተግራ በኩል ደግሞ የቴሌው ዶ/ር ተስፋዬ ብሩ እና የአዋሽ ባንኩን አቶ ለይኩን ብርሃኑን ጨምሮ ጥቂት ሰዎች ወንበር ደርድረው ተቀምጠዋል፡ ፡ እንዳዩኝ የሞቀ ሰላምታ ሰጡኝ፡፡ አይኔን ወደሌላው መለስኩ፡፡ ብቻውን ምድረ ግቢውን ወደሚሽከረከር ሰው፡ ፡ አዎን! ፀሐይዋ አናት የምትበሳ ጉልበታም ብትሆንም የቤንሻንጉል አስተዳደሪ የነበረው ግዙፉ ያረጋል አይሸሹም በእርምጃ ግቢውን በመዞር ስፖርት እየሰራ ነው፡፡ ያልተመጣጠነው ሰውነቱና እንቅስቃሴው ፈገግ ያሰኛል፡ ፡
በዚህ ዞን ማን የቀረ አለ? ‹‹አራጣ አበድራችኋል›› ተብለው የተከሰሱትና በቅፅል ስማቸው የሚታወቁት ሞሮኮ፣ አይ.ኤም ኤፍ…. ካፍቴሪያ ውስጥ ቁጭ ብለው ቡና ይጠጣሉ፡፡ አዛውንቱ የአያት ሪል እስቴት መስራች አቶ አያሌው ተሰማም ብቻቸውን ተቀምጠው ፀሐይ ይሞቃሉ፡፡ ከለበሱት ቱታ በላይ ጋቢ ደርበው፣ የሹራብ ባርኔጣም አጥልቀዋል፡፡ ሙቀቱን እንዴት እንደቻሉት ግራ ገብቶኛል፡፡
ይህን ጊዜም ብስል ቀይ እና እድሜያቸው ስልሳዎቹ መጨረሻ የሚጠጋ አንድ ሰው ፊት ለፊቴ መጡና ጥቂት ትክ ብለው አስተዋሉኝ፡ ፡ እንደዋዛም እንዲህ አሉኝ፡-
‹‹ተመስገን እንተዋወቅ፡፡ መላኩ ተፈራ እባላለሁ፡፡››
‹‹ሻለቃ መላኩ!?….›› በአግራሞት የማረጋገጫ ጥያቄዬን አቀረብኩላቸው፤ ፈገግ ብለው አረጋገጡልኝ፡፡ እርሳቸውም ፍትህ ጋዜጣን አልፎ አልፎ እንደሚያገኙ፣ የእኔን መታሰርም ከውጭ ራዲዮ መስማታቸውን ነገሩኝ፡ ፡ በደንብ አልሰማኋቸውም፡፡ ሻለቃውን በማግኘቴ የተፈጠረብኝ ጥልቅ ግራሞት አለቀቀኝም፡፡ ስለሰውዬው ብዙ ሰምቻለሁ፤ ብዙ አንብቤአለሁ፡ ፡ ታዲያ የሁሉም መደምደሚያ ምን ያህል ጨካኝ እንደሆኑ የሚገልፅ ነው፡ ፡ ሆኖም ከፊት ለፊቴ የቆሙትን አጠር ቀጠን ያሉትን መልከ መልካም ሰው ከተነገረላቸው ታሪክ ጋር ማዛመድ ቸገረኝ፡፡ በአእምሮዬ ውስጥም አንድ ነገር ተመላለሰብኝ፡-
‹‹ሻለቃ መላኩ የእግዜር ታናሽ ወንድም
የዛሬን ማርልኝ ሁለተኛ አልወልድም››
ይህን ያሉት በሻለቃው ጭካኔ በእጅጉ የተማረሩ የጎንደር እናቶች እንደሆኑም ሰምቻለሁ፡፡ እንዲያውም ጎንደር በኢህአዴግ መዳፍ ስር ስትወድቅ፣ ታምራት ላይኔ ይሁን በረከት ስምኦን ዘነጋሁት እንጂ ለዚህ የምሬት ግጥም ‹‹ጎንደር እንዳሻሽ ውለጂ›› የሚል የመልስ ምት በግጥም መስጠታቸውን የኢህዴንን ታሪክ የሚገልፅ መጽሐፍ ላይ አንብቤአለሁ፡፡
እናም የሻለቃው ጭካኔ ወደር እንደሌለው ነው ስሰማ ያደኩት፡ ፡ ስማቸው ድፍን ጎንደርን ያሸብር እንደነበር ነው የማውቀው፡፡ አብዛኞቹ የብአዴን /ኢህዴን/ መስራቾችም በረሃ የገቡት የፖለቲካ አጀንዳ ኖሯቸው ሳይሆን ከሻለቃው ጭፍጨፋ ለማምለጥ እንደሆነ ይወራል፡ ፡ እንዲሁም ዛሬ በአሜሪካ ሀገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መካከል በቁጥር የሚበዙት የጎንደር ተወላጆች መሆናቸውም ከእኚሁ ሻለቃ ለመሸሽ በተደረገ ስደት ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ተደማምረው ነው መሰለኝ እስከዛሬ ድረስ በአእምሮዬ ቀርጬ የያዝኩት የሻለቃው ገፅታ በአካለ-ሥጋ ከፊት ለፊቴ ከቆመው ሰው ጋር አልገጥም አለኝ፡፡ ያውም በብዙ የሚራራቅ፡፡ ግዙፍ ሰውነት፣ እንደመዳፍ የደደረ ከርዳዳ ፀጉር፣ ሞት የሚረጩ ድፍርስ ቀያይ አይኖች፣ በጭካኔ አለት የተገነባ እንደ ድንጋይ የተቸነከረ ፊት፣ ወፋፍራም ደረቅ ከንፈሮች፣ ሠፊ አፍ… በምናቤ ስዬው የኖርኩት የሻለቃ መላኩ ገፅታ ይህ ነበር፡ ፡ እናም ይህ የፈጠርኩት ምስልና በግላጭ የማየው እውነተኛ ምስል ተጣረሱብኝ፤ ማመሳሰል አቃተኝ፡፡ እኚህን ቀለል ያሉ መልከ ቀና ሰው በአንድ ወቅት ‹‹መግደል ሰለቸኝ›› ብለው የሠው ልጅ ከነነፍሱ ሊማሊሞ ገደል ይጨምሩ ነበር የሚለው ታሪካቸውን አምኖ መቀበሉ ከበደኝ፡፡
(ይቀጥላል)